
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ8 ወራት የፖለቲካና የድርጅት ሥራዎችን እቅድ አፈጻጸም በባሕር ዳር ከተማ እየገመገመ ነው።
በግምገማ እና ውይይት መድረኩ ላይ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ እና ሌሎችም የፓርቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
መርሐ ግብሩ በሚኖረው ቆይታ ባለፉት ስምንት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች ቀርበው ጥንካሬ እና ውስንነቶቻቸውን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይም ይመከራል።
የክልሉን ሰላም በማጽናት እና ኅብረ ብሔራዊነትን በመገንባት ሁለንተናዊ እመርታን ለማስመዝገብ የሚጠበቁ ዋና ዋና ሥራዎችም ተነስተው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!