
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን እና አስተያየት እያቀረቡ ነው፡፡ የምክር ቤት አባላቱ ያነሷቸው ጥያቄዎች እና አስተያያቶች፡-
👉 ኢትዮጵያ ያገጠሟት ችግሮች ፖለቲካ ወለድ ናቸው፤ መፍትሔያቸውም ፖለቲካዊ እንጂ ግጭት አይደለም፡፡
👉 በመደማመጥ እና በሰጥቶ መቀበል ላይ ተመሥርቶ ሰላምን ማምጣት ይገባል፡፡
👉 ባለፉት ዓመታት ግጭቶች እና ጦርነቶች ሰዎች ተጎድተዋል፡፡
👉 በጦርነት ምክንያት የሀገር ሀብት እየወደመ ነው።
👉 በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ያልተቋረጡ ግጭቶች ቀጥለዋል፡፡ ግጭት እና አለመረጋጋት ብዙዎች ለችግር እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡
👉 የኑሮ ውድነት ለዜጎች ፈተና ኾኗል፤ ከዚህ ላይ ያለው ግጭት ደግሞ የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ አድርጓል፡፡
👉 የፍትሕ ሥርዓቱ አሁንም ችግር አለበት፤ ከግጭት አዙሪት ካልወጣን ሀገራችን አደጋ ውስጥ እንጥላለን
👉 በአማራ ክልል እና በአሮሚያ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኀይሎች የሰላም ጥሪውን መቀበል አለባቸው፡፡ ለሰላምም ተባባሪ መኾን መቻል አለባቸው
👉 የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ሕዝብ በላቡ የገነባውው የትብብር እና የኅብረት ምሳሌ ነው፣ የአይበገሬነታችንም ምልክት ነው፡፡
👉 የሕዳሴው ግድብ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ ምን ያክል ጊዜ ይቀረዋል?
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!