
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት 6ኛው ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 21ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን እና አስተያየት እያቀረቡ ነው፡፡ የምክር ቤት አባላቱ ያነሷቸው ጥያቄዎች እና አስተያያቶች፡-
✍️ የምክር ቤት አባላቱ መንግሥት የባሕር በር ለማግኘት እያደረገው ያለውን ጥረት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያደንቀው ነው ብለዋል።
✍️ የባሕር በርን ለማስግኘት የዲፕሎማሲ ጥረቶች ቢገልጹልን?
✍️ የባሕር በርን ሰላማዊ እና ፍትሐዊ በኾነ መንገድ ለማግኘት እየተሠራው ያለው ሥራ ቢገልጹን?
✍️ መንግሥት ሰው ተኮር ልማት እንደሚሠራ ካረጋገጠባቸው ሥራዎች መካከል የኮሪደር ልማት ሥራዎች ናቸው።
✍️ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ላይ ሕዝብን የሚያማርሩ እና አፈጻጸማቸው ክፍተት ያለባቸውን ለመቅረፍ ምን እየሠራ ነው?
✍️ መንግሥት ለአርሶ አደሮች ግብዓት ለማቅረብ የሠራው ሥራ የሚያስመሰግን ነው፡፡
✍️ ዘንድሮ የግብዓት አቅርቦት ችግር እንዳይኖር እና መዘግየት እንዳይፈጠር ምን እየተሠራ ነው?
✍️ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚያሳዩ እና የሕዝብን ክብር የሚመጥኑ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ተሠርተዋል፡፡ ለአብነት በቱሪዝም፣ የስካይ ዊን የድሮን ፋብሪካ፣ የአዲስ ኮንቬክሽ ማዕከል፣ እና ሌሎች ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡
✍️ ግብርናውን ለመዛመን ምን እተሠራ ነው?
✍️ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋት ምን እየተደረገ ነው?
✍️ በሀገር ውጭ ያለው የሥራ ስምሪት ምን ያክል ተደራሽ ነው?
✍️ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ መንግሥት ምን እየሠራ ነው፣ ምን ውጤትስ ተገኘ?
✍️ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር መንግሥት ምን እየሠራ ነው?
✍️ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ የመጣው ለውጥ ትልቀ ነው፣ ነገር ግን አሁንም እየተጓተቱ ያሉ አሉ። እነርሱን ለማስተካከል ምን እየተሠራ ነው?
✍️ በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመሰሉም፤ መንግሥት ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት ተማሪዎች እንዲመለሱ ማድረግ ያልቻለው ለምንድን ነው፤ በቀጣይስ ምን ዓይነት የመፍትሔ ርምጃ ሊወስድ አስቧል?
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤት አባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየት ማብራሪያ ይሰጣሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን