ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

24

ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ያቀረቧቸው ጥያቄዎች፦

✍️ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሰላም እፎያታ አስገኝቷል፤ በስምምነቱ መሠረት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የስምምነት ነጥቦቹ በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ፤

✍️ መገዳደል፣ መጠፋፋት እና የፖለቲካ ተቃርኖ ዛሬም ዋጋ እያስከፈለን በመኾኑ መንግሥት እና መሪው ፓርቲ ችግሮችን ሰላማዊ በኾነ መንገድ ተነጋግሮ የመፍታት ባሕል ማጎልበት ላይ በተሰሩ ስራች የተገኘ ውጤት ቢብራር

✍️ የመልሶ ማደረጃት ስራስ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል

✍️ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ከአሥር ዓመቱ ስትራቴጅክ እቅዱ አንፃር ያላቸው አፈፃጸም፣

✍️ በስድስት ወር ውስጥ የመንግስት ወጪና ገቢ ምን እንደሚመስል ቢብራራ፣

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠንካራ የአመራር ቡድን ለዘላቂ ተቋማት ግንባታ ወሳኝ ነው።
Next articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች፡-