
አዲስ አበባ: መጋቢት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም የሸማቾች ቀን “ጥራቱን የጠበቀ ምርት እና አገልግሎት ለሸማቾች” በሚል መሪ መልዕክት እየተከበረ ነው። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ንግድ እና የሸማቾች መብት ጥበቃ መሪ ሥራ አሥፈፃሚ ሊቁ በነበሩ ሸማቾች በኢኮኖሚው ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ብለዋል። ኢኮኖሚው ሚዛኑን ጠብቆ አንዲቀጥል የሸማቾችን መብት ማከበር ይገባል ነው ያሉት።
የሸማቾች መብት እንዲከበርም የአኗኗር ዘይቤ ሽግግር ማድረግ እንደሚያስፈልግም ነው የጠቆሙት። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኀላፊ ሀቢባ ሲራጅ ዕለቱ የሚከበረው የሸማቾችን መብት ለማስከበር ትምህርት እና ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ንፁሕ ምርት እና አካባቢ እንዲኖር እና የመደራጀት መብት እንዲከበር ለማድረግ ነው ብለዋል።
ሸማቾች ለሚያወጧቸው ወጭዎች ተመጣጣኝ አገልግሎት እና አይነት ማግኘት፣ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶች እና ጊዚያቸው ያላለፈባቸውን ምርቶች የመሸመት መብታቸው እንዲከበሩ ዕለቱ ሚናው ትልቅ መኾኑን አንስተዋል።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!