
ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ነገ መጋቢት 11 2017ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ነው ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!