የአሚኮ ደሴ የሚዲያ የግንባታ ለሌሎች ፕሮጀክቶች ምሳሌ መኾን የሚችል በመኾኑ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ገለጹ።

19

ደሴ: መጋቢት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎አሚኮ በደሴ ከተማ እያስገነባ የሚገኘውን ባለ 14 ወለል የሚዲያ ኮምፕሌክስ የአማራ ክልል ምክር ቤት የመንግሥት ወጭ አሥተዳደር እና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢዎች፣ የአማራ ክልል ፕላን እና ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን ወርቅነህን ጨምሮ ሌሎችም ተመልክተዋል።

‎የአማራ ክልል ምክር ቤት የመንግሥት ወጭ አሥተዳደር እና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ እመቤት ከበደ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት የሰው ሃብት አሥተዳደር እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ አበራ ፋንታሁን “የአሚኮ ደሴ የሚዲያ ኮምፕሌክስ የግንባታ ሂደት ለሌሎች ፕሮጀክቶች ምሳሌ መኾን የሚችል በመኾኑ እንደ ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል አጠናክረን እንቀጥላለን” ነው ያሉት።

‎የአማራ ክልል ፕላን እና ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ጥላሁን ወርቅነህ “በክልሉ ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ፕሮጀክቶች እየተጓተቱ ባሉበት በዚህ ወቅት የአሚኮ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታ አሁን የደረሰበት ደረጃ ለሌሎች አካባቢዎች ትምህርት ሊኾን የሚችል ነው” ብለዋል።

‎የአሚኮ ምክትል ሥራ አሥፈጻሚ ህሊና መብራቱ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለማኅበረሰቡ ተደራሽ መኾን የሚችል፣ የቋንቋ ብዝኅነትን የጠበቁ ሥራዎች የሚሠሩበት እና ሀገራዊ አንድነትን ለማምጣት የሚያስችል ትልቅ የሚዲያ ተቋም መኾን እንደሚችል ገልጸዋል።

‎የአሚኮ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታ 44 በመቶ ስለመድረሱ እና በታቀደው ጊዜ ለማጠናቀቅም እየተሠራ ስለመኾኑ ተመላክቷል።

ዘጋቢ:- ፊኒክስ ሀየሎም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኮምቦልቻ ከተማ ፍቅር አንድነት እና ሰላምን የሚያፀና ልዩ የኢፍጣር መርሐ ግብር ተካሄደ።
Next articleበትውልዶች መካከል የሚደረግ የሀገራዊ ምክክር ሂደት።