
ባሕር ዳር: መጋቢት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ “ሰላሜን እጠብቃለሁ ሁለንተናዊ ብልጽግናን አረጋግጣለሁ” በሚል መሪ መልዕክት የጠቅላላ መንግሥት ሠራተኞች የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የዞን፣ የወረዳ መሪዎች እና የመንግሥት ሠራተኞች ለዘላቂ ሰላም እና ብልጽግና ያላቸውን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠይቋል።
የሰሜን ወሎ ዞን የማዕድን መምሪያ ኀላፊ ፈንታው መንግሥቴ ያጋጠሙንን ችግሮች በጋራ በመሥራት ብቻ ማለፍ አለብን ብለዋል። የላስታ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ኢንጅነር ለዓለም ብርሃኑ ሰላም በአንድ ወገን ብቻ የሚመጣ አይደለም፤ የመንግሥት ሠራተኞች ድርሻቸውን በትክክል መወጣት አለባቸው ነው ያሉት።
የላስታ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ጌጡ ሞላ የመንግሥት ሠራተኞች ሕዝቡ ከሰላም ተጠቃሚ እንዲኾን ኀላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል። ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በውይይት መድረኩ የመንግሥት ሠራተኞች በሰላም ማስፈን እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያላቸውን ሚና ማጠናከር እንደሚገባቸው ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!