
ፍኖተ ሰላም: መጋቢት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን እና የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር መሪዎች በከተማ አሥተዳደሩ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። የሥራ ኀላፊዎቹ በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጭ እየተገነባ ያለውን የፍኖተ ሰላም ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ማማሩ ሽመልስ ፕሮጄክቱ ያለበትን ችግር በመቅረፍ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው ብለዋል። ሰላምን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን በመንግሥት እና አጋር አካላት የትምህር ቤት፣ የጤና ጣቢያ፣ የውኃ ማፋሰሻዎች እና የውስጥ ለውስጥ መንገድ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾናቸውን ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አማካሪ ባዬ አለባቸው በችግርም ውስጥ ኾኖ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የሚበረታቱ መኾናቸውን ተናግረዋል። የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!