በ3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ መማሪያ ክፍሎች ተመረቁ።

25

እንጅባራ: መጋቢት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር የሚገኘው ኮሶበር አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኅብረተሰብ ተሳትፎ፣ በእንጅባራ ዩንቨርሲቲ የቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎች በ3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ወጪ 10 መማሪያ ክፍሎችን የያዙ ሕንጻዎች ተገንብተው ለምረቃ በቅተዋል።

በምርቃ መርሐ ግብሩ የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሙሉ አዳም እጅጉ፣ የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የኔዓለም ዋሴ፣ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ደስታው ዓለሙን ጨምሮ የሥራ ኀላፊዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ በአንድ ዓመት ተገንብቶ ስለመጠናቀቁ ተገልጿል።

ዘጋቢ፦ ሰለሞን ስንታየሁ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የባሕር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት የጣና ሐይቅን የበለጠ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያደርግ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ
Next articleየመጀመሪያው የኮሪደር ልማት ተጠናቅቆ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት መጀመሩን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ገለጸ።