
ባሕር ዳር: መጋቢት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከሚመረቱ ምርቶች አንዱ ቅመማ ቅመም ነው። የቅመማ ቅመም ልማት በዞኑ በሚገኙ 15 ወረዳዎች እየለማ ነው። ምዕራብ እና ምሥራቅ ደምቢያ፣ ጣቁሳ እና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች ከፍተኛው ድርሻውን ይይዛሉ።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያ በየነ አያናው እንዳሉት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በ2016/17 የምርት ዘመን 39 ሺህ 969 ሄክታር መሬት በአትክልት እና ቅመማ ቅመም ተሸፍኖ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገኝቷል።
ከዚህ ውስጥ 17 ሺህ 547 ሄክታር መሬት በበርበሬ፣ ነጭ እና ጥቁር አዝሙድ እንዲኹም በነጭ ሽንኩርት ቅመማ ቅመሞች በመሸፈን 226 ሺህ 156 ኩንታል ተገኝቷል።
ከተገኘው ምርት ውስጥ 85 በመቶ ገደማ የሚኾነው በርበሬ ነው። በበርበሬ ከተሸፈነው ውስጥ ደግሞ 2 ሺህ 757 ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም የለማ ሲኾን 60 ሺህ 556 ኩንታል መገኘቱን ገልጸዋል።
የጣቁሳ ወረዳ ደግሞ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል።
በበጀት ዓመቱ በዞኑ በቅመማ ቅመም የታቀደውን ማልማት መቻሉን ገልጸዋል። ሽፋኑም በተለይም ደግሞ የበርበሬ ሽፋን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ባለሙያው ገልጸዋል።
ከባለፈው ዓመትም በሄክታር የሁለት ኩንታል ብልጫ ማሳየቱንም ገልጸዋል።
በዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን