
እንጅባራ: መጋቢት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በጓንጓ ወረዳ፣ በቻግኒ ከተማ አሥተዳደር እና በባንጃ ወረዳ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እና የሌማት ቱሩፋት በክልሉ፣ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ እና በወረዳዎቹ ከፍተኛ መሪዎች ተጎብኝተዋል።
በበጋ መስኖ የለማ ስንዴ ማሳ፣ በሌማት ቱርፋት ከብቶችን የማደለብ እና በወተት ላሞች እርባታ ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች ሥራ፣ ዘመናዊ የመስኖ አውታሮች እና በስጋዲ ሞዴል ችግኝ ጣቢያ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች ናቸው የተጎበኙት።
በበጋ መስኖ ስንዴ ማልማት ባሕል እዬኾነ መምጣቱ ተገልጿል። አርሶ አደሮቹ ተጠቃሚ እንዲኾኑ ዘመናዊ የመስኖ አውታሮችን በመዘርጋት በኩል ጉድለቶች መኖራቸውም ተጠቁሟል።
በቀጣይ በመስኖ ልማት ላይ ያሉ ጉድለቶችን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ስመኾኑም ተነስቷል።
በሌማት ቱሩፋት የደለቡ በሬዎች እና የወተት ላሞችን በማርባት በኩል እየተሠራ ያለው ሥራ ውጤታማ መኾኑን በዘርፉ የተሰማሩ አልሚዎች ገልጸዋል።
ዘመናዊ የመስኖ አውታር ግንባታ ለስንዴ ልማት እና በአካባቢው ለአጠቃላይ የመስኖ ሥራ ጠቀሜታው የጎላ በጉብኝቱ ወቅት ተነስቷል።
ዘጋቢ፦ ሰሎሞን ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!