
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ የርዕሰ መስተዳድሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ ቀለመወርቅ ምኅረቴ፣ የርዕሰ መሥተዳድሩ የመሰረተ ልማት አማካሪ ደሴ አሰሜ፣ የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር)፣ እና ሌሎች አመራሮችም ተገኝተዋል።
አመራሮቹ በሌማት ትሩፋት፣ በእንስሳት እርባታና በወተት ተዋፅኦ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እና ሌሎችንም የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያመለክተው በተፈጥሮ ሀብት ልማት ሥራ እየተከናወኑ ያሉ የተፋሰስ ልማት ሥራዎችንም ጎብኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!