
ወልድያ: መጋቢት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓለሙ ይመር በዞኑ 315 ሺህ 168 የሴፍቲኔት ተጠቃሚ የማኅበረሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ገልጸዋል። በገንዘብ ከ981 ሚሊዮን ብር በላይ እና በእህል ደግሞ ከ196 ሺህ ኩንታል በላይ በዓመት እንደሚሰጥ ነው ያስረዱት።
የሴፍቲኔት ተጠቃሚ የነበሩ እና የተሻለ ሀብት ያፈሩ 32 ሺህ 284 አባዎራዎች ካፈሩት ሀብት ላይ ተጨማሪ ማቋቋሚያ በመስጠት ለማስመረቅ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። በዚህም ለአንድ አባወራ 30 ሺህ ብር በመስጠት ከሴፍቲኔት እንዲመረቁ እየተሠራ ነው ያሉት ኀላፊው ለኘሮግራሙ ማስፈፀሚያ ከ758 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዟል ብለዋል።
ከአሁን በፊት ለኘሮግራሙ ማስፈፀሚያ ለ11 ወረዳዎች 11 መኪናዎችን እና የቢሮ ቁሳቁስ በክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በኩል ከባድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ድጋፍ ተደረጓል ነው ያሉት።
ከ5 ሚሊየን 888 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ 21 ሞተርሳይክሎችም የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ከባድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አማካኝነት ወደ ወረዳዎች እየተሠራጩ መሆኑን ነው የገለፁት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን