
ደብረ ማርቆስ: መጋቢት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ በዞኑ በሚገኙ 18 ከተሞች ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሠረተ ልማቶችን እየሠራ መኾኑን ገልጿል።
ከተሞች ለዜጎች ምቹ፣ ውብ እና ጽዱ እንዲኾኑ መሠረተ ልማቶችን መገንባት እና ዘላቂነታቸውንም ማስጠበቅ ይገባል ሲል የዞኑ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኀላፊ ገዳሙ መኮንን አስገንዝበዋል።
በበጀት ዓመቱ በማኅበረሰብ ተሳትፎ ከ195 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞ የጠጠር መንገድ፣ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ፣ የውኃ ማፋሰሻ ቦይ፣ የመንደር ማስፋፊያ መብራት ዝርጋታ፣ የሥራ እድል መፍጠሪያ ሸድ፣ የአሥተዳደር ቢሮዎች የውኃ መስመር ዝርጋታ እና የወጣቶች መዝናኛ ማዕከላት ሥራዎች በመከናወን ላይ መኾናቸውን ገልጸዋል።
ግንባታዎች በመንግሥት በጀት፣ በረጂ ድርጅቶች እና በማኅበረሰብ ተሳትፎ የሚገነቡ ናቸው።
ኅብረተሰቡ የሚገነቡ ተቋማትን በጥራት እንዲገነቡ መከታተል እና ከተረከበም በኋላ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ እንክብካቤ ማድረግ እንዳለበት ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን