
ባሕር ዳር: መጋቢት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ከእስቴ መካነ ኢየሱስ – ወገዳ ከተማ እየተሠራ የሚገኘው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ እየተሠራ ይገኛል።
የመንገድ ሥራው በወገዳ ከተማ ውስጥ 3 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ቀሪ ሥራዎች ለማጠናቀቅ ነው እየተሠራ የሚገኘው።
የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታው 50 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው። የመንገድ ሥራው ሲጠናቀቅ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን በማሳለጥ የተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮችን ያጠናክራል ተብሏል፡፡
የመንገዱ ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት እና በጥራት እንዲጠናቀቁ በየደረጃው የሚገኘዉ የኅብረተሰብ ክፍል ተገቢውን ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ የዜግነት ግዴታን መወጣት የሁሉም ድርሻ መኾኑን የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን