በባሕር ዳር ከተማ ከአልማ – ዋተር ፍሮንት ሆቴል ድረስ 40 ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ መንገድ ሊሠራ ነው።

31

ባሕር ዳር: መጋቢት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ ከአልማ – ዋተር ፍሮንት ሆቴል ድረስ 40 ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ መንገድ ለመሥራት ቦታውን ከሦስኛ ወገን ነጻ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው። የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የኮሪደር ልማቱ አንድ አካል የኾነ እና ደረጃውን የጠበቀ 780 ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 40 ሜትር ስፋት ኮንክሪት አስፓልት መንገድ ነው የሚሠራው።

ከጣና ነፋሻማ ቦታ አልማ ተነስቶ ወደ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ካምፖስ አቅጣጫ እስከ ዋተር ፍሮንት ሆቴል የሚዘልቀውን አዲስ መንገድ ለመገንባት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቅቀዋል። ከተማ አሥተዳደሩ ከሚመለከታቸው ክፍለ ከተሞች ጋር በመቀናጀት መንገዱ የሚነካቸው 229 የልማት ተነሽዎችን ለይቷል። ተገቢውን የካሳ ግምት በመክፈል እና እና ትክ ቦታ በመስጠት የግንባታ ሥራውን በፍጥነት ለመጀመር 22 ሄክታር የትክ ቦታ አዘጋጅቶ እና ካርታ ሠርቶ ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ነው የተባለው።

በሌላ በኩል የመንገድ ሥራው ዲዛይን የከተማዋን የለውጥ ደረጃ ባገናዘበ መልኩ ተሠርቶ መጠናቀቁን እና የሦስኛ ወገን ተነሽዎችን በተዘጋጀላቸዉ ቦታ እንዲሰፍሩ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር የዝግጁነት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article” የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ጸጋን ጥቅም ላይ ያዋሉ ናቸው” አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)
Next articleየእስቴ – ስማዳ አስፋልት መንገድ ግንባታን ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።