የኅብረት ሥራ ማኅበራትን አገልግሎት የሚያሻሽል ሥራ እየሠራ መኾኑን የፌዴራል ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኮሚሽን ገለጸ።

15

አዲስ አበባ: መጋቢት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኮሚሽን ከክልል እና ከከተማ አሥተዳደር የኅብረት ሥራ ማኅበራት ጋር የ2017 በጀት ዓመት ያለፉት ሥድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው። የተረጋጋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ያለው ማኅበረሰብ ለመፍጠር የኅብረት ሥራ ማኅበራት ጉልህ ሚና አላቸው።

የፌዴራል ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በገጠር እና በከተማ አርሶ እና አርብቶ አደሮች፣ ግብዓት በማቅረብ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ብለዋል። የማኅበራቱን አቅም ለማጎልበት እና ዘላቂነታቸውን በአግባቡ ለማረጋገጥ የለውጥ ማሻሻያዎች እየተሠሩ መኾናቸውን አስገንዝበዋል።

በክልሎች የማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቦት ያለበትን ደረጃ ለመገምገም መድረኩ ዕድል የሚፈጥር መኾኑንም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። ተሻሽለው የሚቀርቡ አዋጆች መሬት ወርደው እንዲተገበሩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ደጋፊ አጋር አካላት በጋራ መሥራት እንደሚገባቸውም አመላክተዋል።

ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ በተገለጸው የውይይት መድረክ ላይ አጋዥ ይኾናል የተባለው የኅብረት ሥራ ማኅበሩ የፖሊሲ ሪፎርም ረቂቅ አዋጅ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

ዘጋቢ፦ ቤተልሔም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበ52 ሚሊዮን ብር የቅርስ ጥገና ሥራ እየተሠራ መኾኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ገለጸ።
Next articleሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በባሕር ዳር ከተማ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረገ።