የአውሮፓ ኅብረት እና የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች በትግራይ ያለውን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተሉት መኾኑን ገለጹ።

35

ባሕር ዳር: መጋቢት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች እና የአውሮፓ ኅብረት በትግራይ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት በጥብቅ እንደሚከታተሉት አስታውቀዋል።

ኢምባሲዎቹ እና ኅብረቱ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2022 የተደረገውን የሰላም ስምምነት እንደሚደግፉ እና ለተግባራዊነቱም የራሳቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ትስስር ገጽ ላይ ያጋራው መረጃ ያመላክታል።

ሁሉም ወገኖች በሰላም መወያየትን መርሕ እንዲያደርጉም ምክረ ሐሳባቸውን ገልጸዋል። ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ድጋፍቸውን እንደሚያጠናክሩም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ

Previous articleበትግራይ ክልል ሕገ ወጡ ቡድን የመፈንቅለ መንግሥት ተግባር መፈጸሙንም አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ
Next articleሕዝብን በልማት ለማስተሳሰር እንደሚሠሩ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞን መሪዎች ገለጹ።