የአማራ ክልል የፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት አሠራሩን ለማዘመን የሚያስችል የልምድ ልውውጥ አደረገ።

16

ባሕር ዳር: መጋቢት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የአማራ ክልል የፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት የበላይ መሪዎች እና የቦርድ አባላት በፌዴራል ፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት፣ በኦሮሚያ ክልል የፍትሕ ባለሙያዎች ማሠልጠኛ ማዕከል የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

የልምድ ልውውጡ ዓላማ የተቋማቱን የአሠራር ሥርዓት መረዳት፣ መልካም ተሞክሮዎችን መለዋወጥ፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እና በጋራ የሚሠሩባቸውን ጉዳዮች ለማመላከት እና እንደ ሀገር ተናባቢ እና ጠንካራ ተቋማት እንዴት መገንባት ይቻላል የሚለውን ለማጠናከር ያለመ መኾኑ ተገልጿል።

በልምድ ልውውጡ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው፣ የአማራ ክልል የፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ደሴ ጥላሁን (ዶ.ር)፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሙሉጌታ አበራ እና ሌሎች የቦርድ አባላት ተሳትፈዋል።

የልምድ ልውውጡ የአማራ ክልል የፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት የያዛቸውን ዘርፈ ብዙ ኀላፊነቶች፣ የለውጥ ጉዞ በተሻለ ተግባራዊ ለማድረግ መልካም ልምድ የሚገኝበት እና ለወደፊት በጋራ ለሚሠሩ ሥራዎችም መሠረት የጣለ መኾኑ ነው የተገለጸው።

የአማራ ክልል ምክር ቤት በቅርቡ የፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የሚያስችል አዋጅ ማጽደቁ ይታወሳል። ይህም ተቋሙ ገለልተኛ እና ጠንካራ የልህቀት ማዕከል እንዲኾን ለማስቻል እንደሚረዳው ተገልጿል።

ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የአደረጃጀት እና የአሠራር ሥርዓቶች ተዘርግተውለታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጤና ባለሙያዎች የጸጥታ ችግር ሳይበግራቸው ማኅበረሰቡ ለተባባሰ የጤና ችግር እንዳይጋለጥ ማድረጋቸውን አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ ገለጹ።
Next article“ኢትዮጵያ ከኩባ ጋር በዋና ዋና ዘርፎች ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት” አቶ አደም ፋራህ