የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከእስራኤል የኢኮኖሚ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።

18

ባሕር ዳር: መጋቢት 04/2017 (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከእስራኤል የኢኮኖሚ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ኒር ባርካት ጋር በኢኮኖሚ ትብብር ፣ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ዙሪያ ተወያይተዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርም በፈጠራቸው የኢንቨስትመንት እድሎች ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ ልዩ ልዩ ሥራ ፈጠራ አማራጮች ፣ የግብርና፣ የውኃ አሥተዳደር ፣ በታደሻ የኃይል አማራጮች እና በአምራች ዘርፍ በኢትዮጵያ ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ በትብብር መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለእስራኤል የቢዝነስ ልዑካን ኢትዮጵያ የንግድ ሁኔታን ለማሻሻል እና የውጭ ኢንቨስተሮችን ለመሳብ የምታደርገው ጥረት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል። የእስራኤል የኢኮኖሚ እና ንግድ ሚኒስትር ኒር ባርካታ እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ጥቅም ላይ ለመሥራት ያላትን ዝግጁነት ገልጸዋል። የእስራኤል ኢንተርፕራይዞች በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሏቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

በውይይታቸው ጥልቅ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትስስርን ለማመቻቸት እና አዳዲስ የትብብር መንገዶችን ለመፍጠር ተስማምተዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሁለቱም ሚኒስትሮች ዘላቂ ዕድገትን፣ የዕውቀት ሽግግርን እና የጋራ ብልጽግናን የሚያራምዱ አጋርነታቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የእናቶች ጤንነት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next articleበደሴ ከተማ በመሠረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈጸመ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።