በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

20

ባሕር ዳር: መጋቢት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት መሠረት ዛሬ በሦስት ቻርተር በረራዎች በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረጓል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአደጋ ሥጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሳዑዲ አረቢያ እና በተለያዩ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከቅጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበ2017/18 የምርት ዘመን ከ47 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት እየሠራ መኾኑን የሰሜን አቸፈር ወረዳ አስታወቀ።
Next articleከ15 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ወጣቶች የሥራ እድል ተፈጥሯል።