በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር የከተማ ግብርና የሴቶችን ተጠቃሚነት እያሳደገ መኾኑ ተገለጸ።

10

ደሴ: መጋቢት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአትክልት እና ፍራፍሬ ምርት ላይ በማተኮር የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር እየሠራ መኾኑን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ገልጿል።

በከተማው የሚገኙ ሴቶች በቡድን ተደራጅተው በአትክልት እና ፍራፍሬ ምርት ላይ በመሰማራት ውጤታማ ኾነዋል።

ቀደም ሲል የቤት እመቤቶች ብቻ የነበሩት እነዚህ ሴቶች በአሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ድጋፍ እና የልምድ ልውውጥ ተሳትፎ በማድረግ ዛሬ ለወጣቶች አርዓያ ኾነዋል።

በከተማ ግብርና ተጠቃሚ የኾኑ ሴቶች ወጣቶች የሚለማ መሬት እያለ ባላስፈላጊ ሱስ መጠመድ እንደማይገባቸው ተናግረዋል። ጥገኛ ከመኾንን ሥራ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። ምርታቸውን ከደላላ ነፃ በማድረግ ለገበያ የሚያቀርቡበት መንገድ እንዲመቻችላቸውም ጠይቀዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ ዓባይነሽ ፍስሀ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ያለውን አቅም መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል። ሴቶችን በማደራጀት ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በትኩረት እየሠሩ እንደኾነም ገልጸዋል። ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የገበያ ትስስር እየፈጠሩ መኾኑንም አብራርተዋል።

192 ሄክታር በአዲስ መስኖ ለማልማት አቅደው 151 ሄክታር መሬት ማልማታቸውንም ገልጸዋል። ከዚህም ከፍተኛ ምርት እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ዘጋቢ፦ ኃይሉ መላክ

📷 :- ተመስገን ስሜነህ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከትርፍም በላይ የሕዝቡን የገበያ ፍላጎት ለመሙላት አስበው እየሠሩ መኾኑን ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ገለጹ።
Next articleየሴቶች የመብት ጥሰትን ለመከላከል እና ሁለንተናዊ ተሳትፎአቸውን ለማረጋገጥ በጋራ መቆም ይገባል።