የኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪያ ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

14

ባሕር ዳር: መጋቢት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪያ ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር አብርሃም መንግሥቱ እና በሚኒስቴሩ የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አዚዛ ገለታ (ዶ.ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበይቻላል መንፈስ መሥራት ከታቻለ ውጤታማ መኾን እንደሚቻል በባሕር ዳር ከተማ የሚኖሩ ስኬታማ ሴቶች ተናገሩ።
Next article“የሐረር አቅጣጫ እና ተስፋ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር)