
እንጅባራ፡ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለሚገኙ ሴት መሪዎች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።
ሥልጠናውን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ከብሔረሰብ አሥተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እና ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያዘጋጁት ነው።
በሥልጠናው በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የተውጣጡ ሴት መሪዎች ተገኝተዋል።
የሴቶች የመሪነት ሚና ሥርዓተ ጾታ እና የሥራ ፈጠራ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችም ሥልጠናው ያተኮረባቸው ጉዳዮች ናቸው።
የሥልጠናው ተሳታፊዎችም ሥልጠናው ሥራ ፈጣሪ እና ጠንካራ ሴት መሪዎችን ለመፍጠር አቅም የሚፈጥር መኾኑንም ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!