
ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዋነኛ ዓላማውም በልዩ አተያይ ሐሳቦችን፣ ለሥራ ተነሳሽነት የሚፈጥሩ ልምዶችን እና ተግባራትን በማካፈል ላይ ያተኮረ ነው።
አልፎ አልፎ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከክልሎች የሚገኙ የሥራ ሪፖርቶችን ለሌሎች የተነሣሽነት ምንጭ እንዲኾኑ ሲሉ ያጋራሉ። በዚህ ሂደት የክልሎች የሥራ ለውጦች ጎላ ብለዉ ይታያሉ፤ በሂደቱም ምርጥ ተመክሮዎች እና ስኬቶች በሌሎች ከፍ ተደርገው እንዲሠሩ ይረዳል።
ይኹን እና ከታችኛው የአሥተዳደር እርከን ጀምሮ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ መረጃዎች በሚፈሱበት ሂደት አንዳንድ ትክክል ያልኾኑ አቀራረቦች በተለያየ እርከን በሪፖርቶች ሊካተቱ መቻላቸውን ትናንት እና በተጋራው መልዕክት ተመልክተናል።
ከዚህ አንፃር በትናንትናው ዕለት በተጋሩ ምስሎች ውስጥ የተወሰኑ ምስሎች ከመስክ ከተገኙ እውነተኛ ፎቶዎች ጋር ተቀላቅላቅለው ከክልል ከነበረ ልውውጥ እስከ ፌደራል ደረጃ ደርሰዋል። ይሄን መሰሉ የመረጃ ፍሰት ስህተት ዳግም እንዳይፈጸም ተገቢ ርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛል።
ምስሎቹን የያዘው ልጥፍ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ገጽ የተነሣ መኾኑንም እየገለጽን ጉዳዩን እንድንመለከት እና ርምት እንዲወሰድ ያሳወቁ ዜጎችንም እናመሰግናለን።
ትክክለኛውን መረጃ እና አቀራረብ የያዙ የተምሳሌታዊው ምርት ሥራ ዘገባዎች በሚዲያዎች የሚቀርቡ መኾኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያሳያል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!