“የኢትዮጵያ እና እስራኤል ግንኙነት ጥንታዊ እና ታሪካዊ መሠረት ያለው እና በጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የተጋመደ ነው” ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር)

29

ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሤ (ዶ.ር) ጋር ተወያይተዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የዲፕሎማሲ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይታቸው በኢትዮጵያን እና እስራኤል መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የእስራኤል የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማሻሻያው የተፈጠረውን የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርበዋል።

“የኢትዮጵያ እና እስራኤል ግንኙነት ጥንታዊ እና ታሪካዊ መሠረት ያለው እና በጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የተጋመደ ነው” ብለዋል።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በእስራኤል የሚኖሩ ከ180ሺህ በላይ ቤተ እስራኤላዊያን ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ቋሚ የግንኙነት መሠረት ናቸው ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሴቶች በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲኾኑ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር አስታወቀ።
Next article“በተሠራው የማስፋፊያ ሥራ ተጨማሪ 310 ሜጋ ዋት ኀይል ማግኘት ተችሏል” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል