“ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን በመቆም ሰላምን ለማጽናት ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ አሳይቷል” መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር)

13

ባሕር ዳር: መጋቢት 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) እንደገለጹት በአማራ ክልል ሕዝብ እና መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተቀናጅተው የሰላም እና የልማት ሥራዎችን እያከናወኑ ነው።

መንግሥት ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ ነው። ለዚህም በሁሉም አካባቢዎች ሕዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል ነው ያሉት።

በውይይቶቹ ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን በመቆም ሰላምን ለማጽናት ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ አሳይቷልም ብለዋል።

ሰላምን ለማስፈን ከሚከናወኑ ሥራዎች ጎን ለጎን የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከሕዝቡ ጥያቄዎች ተነስተዋል። የክልሉ መንግሥትም እነዚህን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት እየሠራ ነው።

ዶክተር መንገሻ ፈንታው በክልሉ ሰላም እና ልማት ጉዳይ ላይ መንግሥት እና ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቅንጅት እየሠሩ ነው ብለዋል።

አሁን ላይ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት ከሚከናወኑ ሥራዎች በተጓዳኝ ሕዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ሰፋፊ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶችም እየተሠሩ እንደኾነ አስረድተዋል።

የክልሉ መንግሥት የተጀመሩት የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ማረጋገጣቸውን ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ግብርና የሀገራችን ምጣኔ ሃብት ዋልታ ነው” ግርማ አመንቴ (ዶ.ር)
Next article“የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን ለአርሶ አደሮች በማቅረብ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ ተችሏል” ወሎ ዩኒቨርሲቲ