ባሕር ዳር: መጋቢት 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያከናወናቸው ባሉ የምክክር ሂደቶች አጀንዳን አግባብነት ባላቸው በተለያዩ መንገዶች እየሰበሰበ ነው፡፡ ኮሚሽኑ በሂደቱ ውስጥ በርካታ አጀንዳዎችን እየተረከበ መኾኑ ተገልጿል።
አጀንዳዎችን ሲረከብ መርሆዎችን በመተግበር መኾኑም ተመላክቷል። የአጀንዳ ሀሳቦች ጥልቀት እና አግባብነት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ላይ ከሀገራዊ ምክክር መርሆዎች እንዱ እንደኾነ ተደንግጓል፡፡ በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች የአጀንዳ ሀሳቦች ጥልቀት እና አግባብነት ዘላቂ መፍትሔን ሊያስገኝ የሚችል እና ውጤታማ የምክክር ሂደቶች ለማድረግ ዓይነተኛውን ሚና ይጫወታል፡፡
የአጀንዳ ሀሳቦች ጥልቀት እና አግባብነት በየትኞቹ መስፈርቶች ይመዘናል?
1. የአጀንዳ ሀሳቦች ጥልቀት
👉 ታሪካዊ ዓውድን መሰረት በማድረጋቸው
👉 የተለያዩ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የፖለቲካ ዘርፎችን ያማከሉ ብሎም ሁለንተናዊ አካታች በመኾናቸው
👉 በመረጃ እና በማስረጃ የተደገፉ በመኾናቸው
👉 ዘለቄታዊና እና በጎ ተፅዕኖን ሊያስከትሉ የሚችሉ በመኾናቸው በሚሉት መስፈርቶች ይለያሉ፡፡
2. የአጀንዳ ሀሳቦች አግባብነት
👉 የሕዝብን እና የሀገርን ጥቅም በማስቀደማቸው
👉 ሀገራዊ ምክክሩ ከቆመለት ዓላማ ጋር መስማማታቸው
👉 ወካይ፣ አስቸኳይ እና አስፈላጊ መኾናቸው
👉 ነባራዊ ሀኔታን እና ዕውነታውን ያገናዘቡ መኾናቸው
👉ግጭትን መቅረፍ መቻላቸው በሚሉት መስፈርቶች ይለያሉ፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን