
ደብረ ብርሃን: የካቲት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እየተከበረ ነው።
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ንጹሕ ሽፈራው ቀኑ ሲከበር የሴቶችን መብት እና እኩል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ብለዋል። የሴቶች መብት እንዲከበር እና እዚህ ለመድረስ የታገሉት ሴቶችን ለማሰብም እንደሚከበር አንስተዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ሴቶች በጋራ ሲሠሩ ከመንደር አልፎ ለሀገርም እንደሚተርፉ ተናግረዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ በለጥሽ ግርማ ሴቶችን በማደራጀት በምጣኔ ሀብት፣ በጤና እና በማኅበራዊ ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲኾኑ እየተሠራ ነው ብለዋል። ይህም የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም በማሳደግ ረገድ መነሳሳትን ይፈጥራል ነው ያሉት።
ቀኑ እየተከበረ የሚገኘው በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የተለያዩ ቀበሌዎች በሚገኙ የሴቶች የልማት ኅብረት ነው። የሴቶች የልማት ኅብረት የሠሯቸው የተለያዩ የልማት ሥራዎችን አሳይተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን