ጠንካራ ሀገር የመገንባት ግብን መሠረት በማድረግ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።

9

ባሕር ዳር: የካቲት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተጠናቅቋል። በሦስት ቀናት ግምገማው የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ውጤታማነትን በጥልቀት ገምግሟል።

በመድረኩ የጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግሥት እና ጠንካራ ሀገር የመገንባት ግቦችን መሠረት በማድረግ ባለፉት 6 ወራት ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸው ተገልጿል። ቀጣይነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባም መግባባት ላይ ተደርሷል ነው የተባለው።

ባለፉት ወራት የፖለቲካ፣ የአደረጃጀት እና የሕዝብ ንቅናቄ ሥራዎች አፈጻጸም በጥልቀት በመገምገም ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባም ተመላክቷል። ስኬቶችን ለማስቀጠል፣ ክፍተቶችን ለመሙላት እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ተጠቁሟል።
በግምገማው በፓርቲው መዋቅር ግንባር ቀደም ተሣትፎ የሚከናወኑ የንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ፣ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ እና ከተረጂነት መላቀቅ ሀገራዊ ግብን ለማሳካት የተሠሩ ውጤታማነት ሥራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም መገንባት ላይ ትኩረት መስጠት ይገባል።
Next articleየሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም መገንባት ላይ ትኩረት መስጠት ይገባል።