ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታስቦ ሲውል የኢኮኖሚ አቅምን መገንባት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።

7

ደብረ ብርሃን: የካቲት 29/2017 ዓ.ም(አሚኮ) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታስቦ ሲውል የኢኮኖሚ አቅምን መገንባት ላይ ትኩረት በማድረግ ሊኾን እንደሚገባ የሰሜን ሸዋ ዞን ሴቶች ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታውቋል።

የመምሪያው ኀላፊ የሮምነሽ ጋሻውጠና በዞኑ በርካታ ሴቶች በኢኮኖሚ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች እየተረፉ ስለመኾኑ ተናግረዋል። ለዚህም በማሳያነት የሚጠቀስ አቅም የፈጠሩ ሴቶችን የሥራ እንቅስቃሴ መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ከክልሉ የተውጣጣ ልዑክን ጨምሮ የዞን ሴት የሥራ ኀላፊዎች በቡልጋ ከተማ አሥተዳደር በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሠማሩ ሴቶችን የሥራ አንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

ለ30 ዓመታት በመምህርነት ያገለገሉት አቻምየለሽ ተስፋዬ በ350 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ሥራ ጀምረው አሁን ላይ በ240 ሚሊዮን ብር ወጭ ፋብሪካ በመገንባት ወደ ተግባር ገብተዋል።

የእኒህን ብርቱ ሴት ተሞክሮ ለሌሎች በማካፈል ሴቶች ወደተሟላ የኢኮኖሚ አቅም ፈጠራ እንዲሸጋገሩ ይሠራል ተብሏል።

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በሰሜን ሸዋ ዞን በተለያዩ መስኮች አርዓያ የኾኑ ሴቶችን የሥራ እንቅስቃሴ የሥራ ኀላፊዎች እየጎበኙ ነው።

ዘጋቢ: ወንዲፍራ ዘውዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleወሎ ዩኒቨርሲቲ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
Next articleየሴቶችን ጥቃት ለመከላከል የሕግ ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባ ተጠየቀ።