ወሎ ዩኒቨርሲቲ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

12

ደሴ: የካቲት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ድግሪ ያሠለጠናቸውን 1ሺህ 320 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ መልዕክት ያስተላለፉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አወል ሰይድ (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም በመማር ማስተማር፣ በምርምር ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በማኅበረሰብ አቀፍ ዘርፎች በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አንስተዋል፡፡ዛሬ ካስመረቋቸው ተማሪዎች መካከልም 317 ያህሉ ሴቶች መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተና ከወሰዱት መካከልም 80 ከመቶ ያህሉ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

የዓለም አቀፍ የውኃ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ እና የምሥራቅ አፍሪካ ተወካይ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ አብዱልከሪም ሁሴን (ዶ.ር) ተመራቂዎች በተለያዩ ፈተናዎች አልፋችሁ ለዚህ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋቸዋል።

በውስብስብ ችግሮች ውስጥ በምትገኘው ዓለማችን ችግሮችን ለመጋፈጥ እና ልዩነት ለማምጣት መጣርና የምትቀይሩት ሕይወት መለኪያችሁ ሊኾን ይገባል ነው ያሉት።

ተመራቂዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በታማኝነት እንዲያገለግሉም አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ:- ደጀን አምባቸው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሕዝብ ውክልናን ለመወጣት የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ አሳሰቡ።
Next articleዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታስቦ ሲውል የኢኮኖሚ አቅምን መገንባት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።