ወልድያ: የካቲት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ በመስክ ምልከታ እየተከበረ ነው። የክልል እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች በጉብኝቱ የተገኙ ሲኾን በከተማው የእንሻሻል የልማት ማኅበር በሥራ ኀላፊዎቹ ተጎብኝቷል።
የማኀበሩ ሰብሳቢ ሃዋ እንድሪስ በማኅበራቸው 30 ሴቶች እንዳሉ ገልጻለች። አንድ ሴት ከ100 ብር ጀምራ ትቆጥባለች። ብድር ከተሰጠው ውጭ 185 ሺህ ብር በአካውንታቸው እንዳለ ገልጻለች። የቁጠባው ገንዘብ ለማኅበሩ አባላት የሥራ መንቀሳቀሻ ብድር ይሰጣል ነው ያለችው።
በሴቶች ቁጠባ በተገኘ ብድር የዶሮ፣ የከተማ ግብርና እና በንግድ ሱቅ ሥራ የተሰማሩ የማኅበሩ አባል ሴቶች ተጎብኝተዋል። ማኅበሩ የጤና፣ የኢኮኖሚ፣ የትምህርት፣ የግብርና፣ የሥራ እድል ተጠሪ እንዳለው የገለጸችው ሰብሳቢዋ እያንዳንዱ ተጠሪ በኀላፊነቱ መሰረት የጤና ግንዛቤ ፈጠራ፣ የሕፃናት እንክብካቤ፣ የቤት አያያዝ እና ሕገ ወጥ ስደት፣ ያለእድሜ ጋብቻ እና መሰል ጉዳዮችን በማኅበራቸው ግንዛቤ እንደሚፈጠር ገልጻለች።
በመደራጀታችን ቤታችን እና ቤተሰባችንን በአግባቡ በመምራት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቤተሰባዊ ችግራችንን ለማቅለል አግዞናል ብላለች። የመርሳ ከተማ አሥተዳደር ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ቀለሟ ብርሃን በከተማ አሥተዳደሩ ደረጃ በ167 የልማት ኅብረት 5 ሺህ 10 ሴቶች ተደራጅተው እርስ በእርስ እንዲረዳዱ መደረጉን ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን