
ባሕር ዳር: የካቲት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ”ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ መልዕክት በደሴ ከተማ እየተከበረ ነው።
በክብረ በዓሉ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሰተባባሪ እና የአማራ ክልል የትምህርት ቢሮ ኅላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች ተገኝተዋል።
ከደሴ ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከፍተኛ መሪዎቹ በተገኙበት በደሴ ከተማ በሞዴል የሴቶች ኅብረት የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!