
ባሕር ዳር: የካቲት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት የመራጭ ተመራጭ የውይይት መድረክ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ዛሬ ደግሞ ከሕዝብ በተነሱ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ላይ ከአማራ ክልል አመራሮች ጋር በባሕር ዳር ከተማ እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ መሠረት ኃይሌን እና በተወካዮች ምክር ቤት የአማራ ክልል ተመራጮች ተገኝተዋል።
በውይይቱ ከሕዝብ የተነሱ ጥያቄዎች ላይ በመወያየት ልማት በሚፋጠንበት፣ በክልሉ ያለው የሰላም እጦት በዘላቂነት በሚፈታበት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን