
ባሕር ዳር: የካቲት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ባለፉት አምስት ዓመታት ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን ማከናወኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል። በተለይም በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ ችግር ምክንያት ለችግር ተጋላጭ ለኾኑ ሴቶች እና ታዳጊ ሴቶች ለመደገፍ ሀብት በማሰባሰብ ድጋፍ ተደርጓል።
ሴቶችን በማሳተፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ:-
👉ለጥቃት የተጋለጡ ሴቶች እና ታዳጊ ሴቶች የቢዝነስ ክህሎት ሥልጠና በመስጠት ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረግ እና ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ ለኾኑ ሴቶች ሁለንተናዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣
👉ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባችው ሴቶች አገልግሎት የሚሰጡ የተቀናጀ የአንድ መስኮት እና የተሃድሶ ማዕከላት ማቋቋም እና ማጠናከር፣
👉አዳዲስ የልማት ኅብረቶች ማቋቋም እና የሴቶች ልማት ኅብረቶች ማጠናከር
👉በኅብረት ሥራ ማኅበራት የተደራጁ ሴቶችን ማጠናከር፣ ሴቶች የብድር ተጠቃሚ እንዲኾኑ በማድረግ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች እንዲሰማሩ ማስቻል፣
👉ሴቶች በተመረጡ ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ በኾኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ ለማድረግ ግንዛቤ መፍጠር፣ ሴቶች በሌማት ትሩፋት ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲኾኑ ማድረግ፣
👉ሴቶች በተለያዩ የሥራ እድል መስኮች ላይ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲኾኑ ማድረግ፣
👉የሴቶችን ማኅበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ለጤናማ እናትነት፣ ሴቶች በጤና ተቋማት እንዲወልዱ፣ የማህጸን በርና የጡት ካንሰርን በሚመለከት ለሴቶች ግንዛቤ መፍጠር፣
👉ታዳጊ ሴቶች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ግንዛቤ መፍጠር፣
👉ሴቶች በሰላም ግንባታ እና ግጭት አፈታት ዙሪያ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ በአጎራባች ክልሎች መካከል እንዲሁም በክልሎች ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች የእርስ በእርስ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲያደርጉ ማመቻቸት፣
👉ሴቶች “ቡና ለሰላም” በሚል መርሕ በአካባቢያቸው ለሰላም ግንባታ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ፣
👉ሴቶች በአገራዊ ምክክር እና በሽግግር ፍትሕ እንዲሳተፉ ማድረግ
👉ሴቶች በበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሳተፉ ማድረግ፣
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን