
አዲስ አበባ: የካቲት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት “ዓላማ ተኮር፣ የተናበበ እና የተቀናጀ የተግባቦት ሥርዓት ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ መልዕክት የስድስት ወር የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ተግባራት አፈጻጸም በአዳማ ከተማ እየገመገመ ነው።
በመድረኩ የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በስድስት ወራት ያከናወናቸው ተግባራት በቢሮ ኀላፊው መንገሻ ፈንታዉ (ዶ.ር) በተሞክሮነት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።
የተሞክሮ ሰነዱን ያቀረቡት የቢሮ ኀላፊዉ በተቀናጀ እና በተናበበ መንገድ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ተግባር በመከወናችን በክልሉ የተፈጠረውን ቀውስ ቀልብሰን በአንጻራዊነት ወደ ሰላም እንዲመጣ የድርሻችን ተወጥተናል ብለዋል።
ለአንድ ሀገር እድገት እና ብልጽግና ሚዲያ ወሳኝ ነው ያሉት ኀላፊው ዘመኑን የሚመጥን የሚዲያ ኮሙኒኬሽን ተግባር በመከወን ቀጣይ በተሟላ ደረጃ የክልሉን አጠቃላይ ገጽታ ለመቀየር እንሠራለን ብለዋል።
በግምገማው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር)፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የሚዲያ መሪዎች እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ የስድስት ወራት የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ተግባራትን በመገምገም የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን