የከተማ የመስኖ ልማት ልምድ እያደገ መኾኑን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች ገለጹ።

4

ወልድያ: የካቲት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከምንግሥት የተጠናከረ ድጋፍ ካገኙ የከተማውን የመስኖ ልማት ልምድ የማሳደግ አቅም እንዳላቸው የወልድያ ከተማ አሥተዳደር አርሶ አደሮች ተናግረዋል። በከተማ አሥተዳደሩ እየተሠራ ያለ የመስኖ ልማት ተጎብኝቷል። በመስክ ጉብኝቱ ላይ ያገኘናቸው አርሶ አደሮች ቋሚ አትክልት እና ፍራፍሬ፣ የአጭር ጊዜ አትክልት ዝርያ እና የበጋ መስኖ ስንዴ እያለሙ እንደሚገኙ ነግረውናል።

አርሶ አደሮች ከተማ አሥተዳደሩ የስንዴ ዘር፣ የአትክልት ዘር እና ማዳበሪያ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዳቀረበላቸውም ነው የጠቆሙት። ውኃን ከወንዝ ለመጥለፍ ይቻል ዘንድ በኩታ ገጠም እየተቀናጁ የውኃ ፓምኘ በዝቅተኛ ዋጋ ከተማ አሥተዳደሩ አቅርቦልናል ብለዋል።

በመስኖ ልማት ተጠቃሚ መኾናቸውን የተናገሩት አርሶ አደሮቹ ከተማ አሥተዳደሩ ተከታታይ ድጋፍ የሚያደርግላቸው ከኾነ የከተማውን የመስኖ ልማት ልምድ የመቀየር አቅም እንዳላቸው አስረድተዋል። የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ ደስታ ሞላ ከ64 ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ እየለማ ነው ብለዋል።

የከተማ አሥተዳደሩ የውኃ ፓምኘ፣ የግብዓት እና የሙያ ድጋፍ ለአርሶ አደሮቹ እያደረሰ መኾኑንም ነግረውናል። የወንዞችን ሙሉ አቅም ለመጠቀም ይቻል ዘንድ ተጨማሪ የውኃ ፓምኘ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር እናሰራጫለን፤ ሙያዊ እና የግብዓት እገዛችንም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየእንስሳት ኢንሹራንስን ተግባራዊ ማድረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next article“ሴቶች ምጣኔ ሀብታዊ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ በልማት ሥራዎች ላይ ማሳተፍ ይገባል” የሰሜን ጎጃም ዞን