
ባሕርዳር: የካቲት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በነባሩ ጭልጋ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የነባሩ ጭልጋ ወረዳ ምክትል አሥተዳዳሪ ሰለሞን እያዩ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ ግል ሕይወታችሁ መመለሳቸውን ተናግረዋል። ገብተውበት የቆዩት የተሳሳተ መኾኑን በመረዳት ፣ ወደ ኅብረተሰቡ በመቀላቀል እራቸውን እና አከባቢያችሁን ማልማት እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል።
የነባሩ ጭልቃ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሀሰን ሱሩር መንግሥት የሰጠውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደሰላም በመምጣታችሁ ለራሳችሁና ለአከባቢው ሰላምና ልማት ውሳኝነት አለው ብለዋል።
ሌሎችም ታጣቂዎችም ወደሰላም እንዲመለሱ ጠይቀዋል። መንግሥት የሰላም በሩ ክፍት መኾኑንም ተናግረዋል።
ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ መኾናቸውን ገልጸዋል። ሌሎችም የሰላም አማራጩን እንዲቀበሉ እንሠራለን ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!