የሴቶችን ተጋላጭነት በመቀነስ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡

7

ፍኖተ ሰላም: የካቲት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ፤ በኢኮኖሚ ላይ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማድረግ ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሻለ እንቅስቃሴ ያላቸው ሴቶችን ወደ ፊት በማምጣት እና ዕውቅና በመስጠት ሌሎች ሴቶችም አርዓያቸውን እንዲከተሉ ፋይዳው የጎላ ነው።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ሴቶች ፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሴቶች ቀንን ባከበረበት ወቅት በተለያዩ ዘርፎች ሞዴል የኾኑ ሴቶችን ዕውቅና ሰጥቷል። ይህ ዕውቅና ደግሞ ሴቶችን በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ነው የመምሪያው ኀላፊ ስለእናት ዘሪሁን ተናግረዋል።

በዞኑ 2ሺህ 400 የሚኾኑ ሴቶች በቁጠባ ማኅበራት ውስጥ በመግባት እስከ 20 ሚሊዮን ብር መቆጠብ እንደቻሉ ገልጸዋል። የሴቶችን ተጋላጭነት በመቀነስ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ሁሉም ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።

ዕውቅና የተሰጣቸው ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ እዳይኾኑ የሚያግዳቸው ነገር የለም ነው ያሉት። ዕውቅና የተሰጣቸው ሴቶችም የተሳሳቱ እሳቤዎችን በመተው ዓላማቸው ላይ ትኩረት በማድረግ መሥራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

አሁንም ቢኾን በማኅበረሰቡ ዘንድ ለሴቶች እየተሰጠ ያለው እሳቤ በሚፈለገው ልክ አይደለም ተብሏል። የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ማኅበረሰቡ አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚገባም ተመላክቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመንግሥትን አጀንዳዎችን የማስረጽ ሥራው ውጤታማ መኾኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
Next articleበአማራ ክልል የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሠራ ነው፡፡