በኮምቦልቻ ከተማ የኢንዱስትሪ እና የፋይናንስ ኤክስፖ ሊካሄድ ነው።

11

ባሕር ዳር: የካቲት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማን የኢንዱስትሪ ከተማነት ለማሳደግ በማለም ከሚያዝያ 20 እስከ 29/2017 ዓ.ም የሚቆይ ሀገር አቀፍ የኢንዱስትሪ እና የፋይናንስ ኤክስፖ ለማዘጋጀት እየሠራ መኾኑን ከተማ አሥተዳደሩ አስታውቋል።

ኤክስፖው “ሰላም የኢንቨስትመንት ፓስፖርት ነው” በሚል መሪ መልዕክት ነው የሚዘጋጀው። ዝግጅቱን በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሐመድአሚን የሱፍ ኤክስፖው ከተማዋን የበለጠ ለማዘመን የሚያስችል ነው ብለዋል። አዳዲስ አልሚ ባለሃብቶችን ለመሳብም ያስችላል ነው ያሉት።

በከተማዋ ለሚገኙ ባለሀብቶች ደግሞ የተሻለ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ገልጸዋል ። ኤክስፖው የአካባቢውን ፀጋ በመጠቀም የከተማዋን የመልማት ፍላጎትም ያሳድጋል ብለዋል ከንቲባው። ሸማቹን እና ሻጩን ከማገናኘት ባለፈ የእርስ በርስ ትስስርን በማጠናከር የማኅበረሰቡን በጋራ የመልማት አቅም ያሳድጋል ነው ያሉት።

ኤክስፖው የጋራ አንድነትን ይፈጥራል፤ አብሮነትን ያጎለብታል። አኹን ላይ ያለው ሰላም ወደ አካባቢው ለሚመጡ እንግዶች የማኅበረሰቡን እሴቶች ለማስተዋወቅ ምቹ መኾኑን ከንቲባው ገልጸዋል። ከተማ አሥተዳደሩ ከአኹን በፊትም ለአልሚ ባለሀብቶች ምቹ ኹኔታዎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ከንቲባው በመግለጫቸው አንስተዋል።

ዘጋቢ:- ኃይሉ መላክ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግን ጎበኙ።
Next articleሴቶች በማኅበር በመደራጀት የቁጠባ ባሕላቸውን እያሳደጉ መኾኑ ተገለጸ።