“በክልላችን በሚገኙ ሰባት ከተሞች የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

21

ባሕር ዳር: የካቲት 2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን ከተሞች የሥራ አፈጻጸም ገምግመዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የከተማና መሠረት ልማት ሚኒስቴር መሪዎች በተገኙበት የክልላችን ከተሞች የበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ገምግመናል ብለዋል።

ባለፉት ወራት የዘርፉን ተቋማት በማስተሳሰር እና ሕዝብ በማሳተፍ የከተሞችን ጥራትና ደረጃቸውን ለማሻሻል በርካታ ሥራዎችን ሰርተናል ነው ያሉት።

በክልላችን በሚገኙ ሰባት ከተሞች የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል። ሕዝብን በማስተባበር የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ወደ ሌሎች ከተሞች ለማስፋት አቅደው እየሠሩ መኾናቸውን ተናግረዋል።

የክልላችን ከተሞች በፕላን የሚመሩ ዘመናዊነትን የተላበሱ፣ ለኑሮ ምቹ፣ ጽዱ፣ ውብና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ የጀመርነውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት።

የክልላችን ከተሞች የማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማሳለጫ፤ የምርት፣ የንግድና የገበያ ማዕከለንታቸውን የበለጠ ውጤታማ እንዲሆንም በቅንጅትና በትጋት እንሠራለን ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleማይክሮሶፍት ስካይፕን ሊዘጋ ነው
Next articleየማኀበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት በጥራት እና በፍትሐዊነት ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስታወቀ።