
ደሴ: የካቲት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ”አብሮነት ለበጎነት በረመዳን” በሚል መሪ መልዕክት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደሴ ዲስትሪክት የተዘጋጀ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር በደሴ ከተማ ተካሂዷል።
ባንኩ በከተማዋ በአምስቱም ክፍለ ከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 150 የኅብረተሰብ ክፍሎች ነው ድጋፍ ያደረገው። 750 ሺህ ብር ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ነው ድጋፍ የተደረጉት።
ድጋፍ የተደረገላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችም በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስለተደረገላቸው እገዛም ምሥጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ተጠባባቂ ዳይሬክተር መብራቴ ሞላ የድጋፉ ዓላማ ባንኩ ለማኅበረሰቡ ያለውን አጋርነት ለመግለጽ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
በደሴ ከተማ የተካሄደው ድጋፍ ጅማሮ መኾኑን የገለጹት ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ በቀጣይ በተለያዩ አካባቢዎች ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ፊኒክስ ሀየሎም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን