በጫካ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።

20

ባሕር ዳር: የካቲት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጫካ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ተቃጣቂዎች ከጦርነት ይልቅ ሰላምን በማስቀደም ጥሪውን መቀበላቸውን ገልጸዋል። መንግሥት ባቀረበው የሰላም ጥሪ መሠረት ጥሪውን ስንቀበል ያለምንም ችግር አቀባበል ተደርጎልናል ብለዋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኀላፊ አለልኝ ዓለም በከተማዋ በጫካ ይኖሩ የነበሩ በርካታ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እየገቡ መኾናቸውን ተናግረዋል።

ከጦርነት ይልቅ ሰላም እና ልማት ይበልጣል ያሉት ኀላፊው ዛሬ ስምንት ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ገልጸዋል።

መንግሥት አሁንም ለሰላም ዝግጁ መኾኑን አመላክተዋል። ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩንኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በጫካ የሚኖሩ ታጣቂዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመቀበል ዝግጁ መኾናቸውንም አመላክተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኀላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ መልእክት:-
Next articleየኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለሦስት ከተሞች የቢዝነስ ፖርታሎችን አስመረቀ።