በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኀላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ መልእክት:-

21

ብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት ዓመት ያለፉት ወራት የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም የምንገመግምበት እና ሌሎች በፓርቲ መዋቅር ግንባር ቀደም ተሳትፎ የሚከናወኑ የንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ የምንመክርበት መድረክ በዛሬው ዕለት ጀምረናል።

መድረኩ የጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግሥትና የጠንካራ ሀገር ግንባታ ግቦቻችንን መሰረት በማድረግ ባለፉት ወራት የሠራናቸውን የፖለቲካ፣ የአደረጃጀት እና የሕዝብ ንቅናቄ ሥራዎች አፈፃፀም በጥልቀት የምንገመግምበት እንዲሁም ስኬቶችን አስፍቶ ለማስቀጠል፣ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የጀመርናቸው የንቅናቄ ተግባራትን በሚመለከታቸው አካላት ዘንድ ባሕል እንዲሆኑ ለማድረግ እና በቀጣይ በበጀት ዓመቱ የያዝናቸውን እቅዶች በመፍጠር እና መፍጠን በተሟላ መልኩ በውጤታማነት ለማሳካት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን የሚናስቀምጥበት ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበወልድያ ከተማ በሚሠሩ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡ ተሳትፎ እና ተባባሪነት የሚበረታታ መኾኑ ተገለጸ።
Next articleበጫካ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።