
ባሕር ዳር: የካቲት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በወልድያ ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ.ር) የከተማዋን መሠረተ ልማት ለማሟላት እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች የሚበረታቱ መኾናቸውን ገልጸዋል።
ከተማዋን ለቱሪዝም፣ ለኢንቨስትመንት ሳቢ እና ማራኪ፣ ለኖሪዎቿም ምቹ ለማድረግ በከተማ አሥተዳደሩ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች በጥሩ ሂደት ላይ መኾናቸውን ተናግረዋል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ከተማው ውስጥ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የፕሮጀክቶች ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
አብዛኞቹን ፕሮጀክቶች እስከ መጋቢት 30 2017ዓ.ም እንዲጠናቀቁ ታስቦ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ኅብረተሰቡ በሚሠሩ የተለያዩ ልማቶች ላይ የሚያሳየው ተሳትፎና ተባባሪነት የሚያስደስት ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በቀጣይም ማኅበረሰቡ በዕውቀት በገንዘብ እና በጉልበት የሚችለውን በማድረግ የኮሪደር ልማቱ ላይ እንዲሳተፍ ጠይቀዋል።
ከወልድያ ከተማ ኮምዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የሰላሳ ሜትር የቀለበት መንገድ ፕሮጀክት፣የንግድ ማዕከል ግንባታ፣ የቤተ መጻሕፍት ግንባታ እና የኮሪደር ልማት ሥራን ጎብኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!