
ባሕር ዳር: የካቲት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ከኦሮምያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ጋር በአምቦ ወረዳ በነበራቸው ጉብኝት የኬኛ ቤቭሬጅ ፋብሪካን ተመልክተዋል። ፋብሪካው በመጪዎቹ ሦስት ሳምንታት ውስጥ ወደሥራ ይገባል ተብሏል።
የአሥተዳደር ሥራን ወደ ሕዝብ ለማቅረብ የቀበሌዎች መጠናከር ወሳኝ ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በየአካባቢው ለሕዝብ ቅርብ የሆነ አሥተዳደር ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ነው ተብሏል። በአምቦ ወረዳ የአንድ ቀበሌ እንቅስቃሴ በጉብኝት ወቅት ታይቷል። በዚህ ቀበሌን የማብቃት ተግባር በክልሉ 7342 ቀበሌዎች ተደራጅተዋል ነው የተባለው። 50 ሺህ የሰው ኀይል እንደተመደበላቸውም ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም በወረዳዎች ተማክለው የነበሩ ሞያዊና አሥተዳደራዊ አገልግሎቶች በቀበሌ ደረጃ በተገቢው የሰው ኀይል እየተሰጡ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወንጪ ደንዲ ኤኮ ሎጅ አካል የሆነው የደንዲ ክፍል ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የሥራው የሲቪል ግንባታ ሥራዎች ምዕራፍ ተጠናቆ አሁን የማጠናቀቂያ ሥራዎች በመሠራት ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!