“ጣናን ከልሎ የነበረው ጢሻ ተገላልጦ የሐይቁ ድብቅ ውበት ፍንትው ብሎ መመልከት ሀሴትን ያጎናፅፋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

36

ባሕር ዳር: የካቲት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ባሕር ዳር ኅብረተሰቡ በሚዝናናባቸው መናፈሻዎች፣ ብስክሌት በነጻነት ማሽከርከር በሚያስችሉ ሰፋፊ መንገዶች እየተዋበች ነው ብለዋል።

ጣናን ከልሎ የነበረው ጢሻ ተገላልጦ የሐይቁ ድብቅ ውበት ፍንትው ብሎ መመልከት ሀሴትን ያጎናፅፋል ነው ያሉት።

ለአገልግሎት ክፍት የሆኑትም ኾነ በሂደት ላይ የሚገኙ የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራዎች፣ በዘላቂነት ለረጅም ዓመታት እንዲያገለግሉ ኅብረተሰቡ በባለቤትነት መንፈስ ሊጠብቃቸው እና ሊንከባከባቸው ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየብልጽግና ፓርቲ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ።
Next articleበሁመራ ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች የሚበረታቱ መኾናቸው ተገለጸ።