
ባሕር ዳር: የካቲት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የግብር ከፋዩን ማኅበረሰብ ጊዜ እና ጉልበት ሊቆጥብ የሚያስችል አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አሥተዳደር ሥርዓት ፕሮጀክት ይፋዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም በኮምቦልቻ ከተማ አካሂዷል።
የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ዘመናዊ እናደርጋለን ያሉት የገቢዎች ቢሮ ኀላፊ ክብረት መሐመድ ፕሮጀክቱን በመደገፍ እና በመከታተል አስፈላጊውን ግብር መሰብሰብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ይህ ፕሮጀክት ቀደም ብሎ በባህር ዳር ከተማ ተሞክሮ ውጤታማ በመኾኑ ዛሬ ላይ በደቡብ ወሎ ዞን የሙከራ ትግበራ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት መካሄዱን ተናግረዋል።
አዲስ የበለጸገው ፕሮጀክት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ወደ ተግባር የገባ መሆኑንም ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ግብር ከፋዩ ማኅበረሰብ ካለበት ቦታ ሆኖ የሚጠበቅበትን ክፍያ መፈጸም የሚያስችል እና ደረሰኙንም ማግኘት የሚያስችል ነው ያሉት ደግሞ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዌብሳይቱ አበልጻጊ አባል አሰፋ ምስጋናው ናቸው።
ይህ መኾኑ ቀልጣፋ እና ታማኝነት ያለው አገልሎት ለመስጠት ያስችላልም ብለዋል።
ዘጋቢ: ኃይሉ መላክ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!